የምርመራ ጓንት (Examination glove) ፍላጎት በሀገር ዉስጥ ምርት እየተሸፈነ መሆኑ ተገለፀ
አገልግሎቱ በከፍተኛ መዋለ ንዋይ ከአለም አቀፍ አምራቾች ከሚያስገባቸው የህክምና መገልገያዎች መካከል የምርመራ እና የህክምና ጓንት (Examination and Surgical glove) ይገኙበት የነበረ ቢሆንም የምርመራ ጓንት ፍላጎት በሀገር ውስጥ ምርት መሸፈን እንደተቻለ መሆኑን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ሰሞኑን ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ጋዜጣዊ መገለጫ ላይ ገልፀዋል
